ዩክሬን እና አውሮፓ ሞስኮ ላይ ውስብስብ እና ደም አፋሳሽ ትንኮሳዎችን ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ
14:59 16.06.2025 (የተሻሻለ: 15:04 16.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩክሬን እና አውሮፓ ሞስኮ ላይ ውስብስብ እና ደም አፋሳሽ ትንኮሳዎችን ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ
ይህ እየሆነ ያለው ዩክሬን በጦር ግንባር ችግሮች እየተባባሱባት እና "የዩክሬን ማሕበረሰብ ከመጋረጃ ጀርባ የሞራል ድካም" በገጠመው ጊዜ ነው ብሏል አገልግሎቱ በመግለጫው።
የስለላ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ዩክሬናውያን ከብሪታኒያ ጋር በመሆን በባልቲክ ባሕር ላይ ትንኮሳ ለመሠንዘር እየተዘጋጁ ነው ብሏል። ከሁኔታዎች አንዱ በዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል መርከብ ላይ በሩሲያ የሚላከክ የቶርፔዶ ጥቃት መፈጸምን ያካትታል።
የዩክሬን ወገን የሶቪየት-ሩሲያ ቶርፔዶዎችን ለእንግሊዞች አስረክቧል። አንዳንዶቹ ከአሜሪካ መርከብ “በአስተማማኝ ርቀት” እንዲፈነዱ የታቀደ ሲሆን አንደኛው ግን እንደማይፈነዳና ለሩሲያ “የጥፋት ተግባር” ማስረጃ ሆኖ ለሕዝብ እንደሚቀርብ አገልግሎቱ ግልጿል፡፡
የዩክሬን የጸጥታ ኃይሎች እቅዱን ለማስፈጸም መዘጋጀታቸውንም ነው መግለጫው ያመለከተው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X