ኤርዶአንና ፑቲን የስልክ ውይይት አደረጉ
14:11 16.06.2025 (የተሻሻለ: 15:04 16.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኤርዶአንና ፑቲን የስልክ ውይይት አደረጉ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት እና የቱርክ አቻቸው በእስራኤል እና ኢራን ግጭት ዙሪያ መምከራቸው የቱርክ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።
ኤርዶአን እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ የተባባሰው የኃይል እርምጃ አጠቃላይ የቀጣናውን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቱርክ እስራኤል በኢራን ላይ የምትሰነዘረውን ጥቃት ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ ተነሳሽነቶች ላይ ማተኮሯን ለሩሲያው መሪ አሳውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X