ሩሲያ የኢራን - እስራኤልን ግጭት ለማሸማገል ዝግጁ ናት ሲል ክሬሚሊን አስታወቀ
13:34 16.06.2025 (የተሻሻለ: 13:54 16.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የኢራን - እስራኤልን ግጭት ለማሸማገል ዝግጁ ናት ሲል ክሬሚሊን አስታወቀ
ፑቲን በቅርቡ ለትራምፕ ያቀረበት የሞስኮ እቅድ አሁንም ጠረጴዛው ላይ እንደሆነና ሊተገበር እንደሚችል የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከክሬምሊን የተገኙ ተጨማሪ ሀሳቦች፦
▪ ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት እንዲባባስ ያደረጉ ድርጊቶችን ታወግዛለች።
▪ ሩሲያ የኢራንን ከመጠን ያለፈ የኒውክሌር ቁሳቁስ ለማስወገድ ያቀረበችው ሀሳብ አሁንም ተገቢነት አለው።
▪ በመካከለኛው ምሥራቅ በተባባሰው ግጭት ምክንያት በአየር ትራፊክ ላይ የተጣሉት እገዳዎች የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም 2025 ከፍተኛ እንግዶች በመድረኩ የመገኘት እድላቸው ላይ ተፅዕኖ እንደማይኖረው ሩሲያ ተስፋ ታደርጋለች።
▪ ፑቲን ለሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል፤ በፎረሙ የመክፈቻ ንግግራቸውን ዓርብ ያደርጋሉ።
▪ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል አዲስ ዙር ድርድር የሚካሄድበት ትክክለኛ ቀን ገና አልተወሰነም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X