የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊ በ "LGBT" የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ቀሳውስትን በማሰሯ ሞልዶቫን በማውገዝ፤ ሀገሪቷ ለ"ውጫዊ ጫና" ተጋልጣለች አሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊ በ "LGBT" የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ቀሳውስትን በማሰሯ ሞልዶቫን በማውገዝ፤ ሀገሪቷ ለ"ውጫዊ ጫና" ተጋልጣለች አሉ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊ በ LGBT የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ቀሳውስትን በማሰሯ ሞልዶቫን በማውገዝ፤ ሀገሪቷ ለውጫዊ ጫና ተጋልጣለች አሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.06.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊ በ "LGBT" የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ቀሳውስትን በማሰሯ ሞልዶቫን በማውገዝ፤ ሀገሪቷ ለ"ውጫዊ ጫና" ተጋልጣለች አሉ

“በሞልዶቫ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን የኦርቶዶክሳውያንን መንፈሳዊ ማንነት ለመለወጥ፣ የሥርዓተ-ፆታ አስተሳሰብ ለመጫን እና በመጨረሻም የባሕላዊ ቤተሰብ ጽንሰ-ሀሳብን ለማጥፋት የሚደረጉ ሙከራዎችን እንደሚቃወሙ የመግለጽ መብት አላቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሲኖዶስ የመገናኛ ብዙኃን ግንኙነት ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ ቫክታንግ ኪፕሺዜ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በኪሺኔቭ እየተካሄደ ያለውን የ"LGBT"* ተቃውሞ ሰልፍ በመጥቀስ፤ የሞልዶቫ ሕዝብ “ንቃተ ህሊናን በግዳጅ የመቅረፅን እና እነዚህን ከሥነ ምግባር የራቁ አመለካከቶችን የመቃወም” መብት አለው ሲሉ ሞግተዋል።

አክለውም የሞልዶቫ መንግሥት “ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋር የተሳሠረውን የሞልዶቫ ሕዝብ ማንነት ለመቀየር ፍላጎት ባላቸው የውጭ ኃይሎች” ተጽዕኖ ሥር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህን “ባዕድ” የሥርዓተ-ፆታ አመለካከትን መጫን ሞልዶቫን “ከክርስትና ጋር የማይጣጣሙ እሴቶች” ወደተዛመተባት ሀገር የመቀየር አደጋ ያለውና ብሔራዊ እና ሐይማኖታዊ ማንነቷን እንድታጣ ያደርጋታል ብለዋል።

*በአክራሪነት የተፈረጀ እና በሩሲያ የታገደ እንቅስቃሴ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0