የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እንዲጠቀሙ ተጠየቀ
18:08 15.06.2025 (የተሻሻለ: 18:24 15.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እንዲጠቀሙ ተጠየቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እንዲጠቀሙ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና እሁድ የኤአይ ስቱዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት አጠቃቀም ዙሪያ ያሰለጠኗቸውን 25 የሚዲያ ባለሙያዎች አስመርቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ቴክኖሎጂውን በመገናኛ ብዙኃን የይዘት ሥራዎች ውስጥ በመጠቀም ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ማዋል እንደሚገባ አጽዕኖት ሰጥተዋል።
ሰልጣኞቹ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቁ ፊልሞችን በማምረት፣ ሌሎች ሙያተኞችን በማሰልጠን፣ ስለ ቴክኖሎጂው ግንዛቤ ለመፍጠር መሥራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እንዲጠቀሙ ተጠየቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/