የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በሞልዶቫ "LGBT" ሰልፍን በተቃወሙ ቄሶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘች

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በሞልዶቫ "LGBT" ሰልፍን በተቃወሙ ቄሶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘች

"የLGBT* ኩራት ሰልፍን በተቃወሙ የሞልዶቫ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ቀሳውስት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እናወግዛለን። በሞልዶቫ ሕብረተሰብ ላይ ባሕላዊውን የቤተሰብ ስርዓት ለማጥፋት የጾታ አስተሳሰብን የመጫን እንቅሰቃሴ የፖለቲካ ሳይሆን የሞራል ጉዳይ ነው። ቤተ-ክርስቲያንም ሆነ ሌሎች ለእውነት የቆሙ የማሕበረሰብ ኃይሎች በዚህ ፀረ-ክርስትና ፕሮጀክት ላይ መተባበር አለባቸው" ሲሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ተወካይ ተናግረዋል።

"መጀመሪያ ላይ የአናሳዎችን መብት ማስጠበቅ መስሎ የተጀመረው እንቅስቃሴ በምዕራባውያን ሀገራት ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ጥንዶች ልጅ የሚያሳድጉበት፣ ፀረ-ቤተሰብ ውሸቶችን በትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚካተትበት እና በመጨረሻም ልጆች ጾታቸውን የመቀየር ደረጃ ላይ መድረሱን እናውቃለን" ሲሉ አክለዋል።

"የሞልዶቫ አማኞች በእናት ሀገራቸው እንደዚህ አይነት ነገሮች እንዲፈጸሙ እንደማይፈቅዱ ተስፋ አደርጋለሁ። የሞልዶቫን ሕዝብ መንፈሳዊ ወግ እንዳይጠፋ ለመከላከል ለሚጥሪ የኦርቶዶክስ አማኞች እንጸልያለን" ብለዋል።

*በአክራሪነት የተፈረጀ እና በሩሲያ የታገደ እንቅስቃሴ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0