የሰሜን አፍሪካ ሀገራት እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት አወገዙ
19:39 14.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 14.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሰሜን አፍሪካ ሀገራት እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት አወገዙ
የአልጄሪያ፣ የቱኒዚያ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የእስራኤልን ድርጊት የሚቃወም መግለጫ ያወጡ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት አስቸኳይ ጥረት እንዲያደርግ አሳስበዋል።
በመግለጫዎቹ የተካተቱ ይዘቶች፡-
አልጄሪያ የእስራኤል ጥቃት ከዚህ በፊት ለተፈፀሙ ጥቃቶች "ቅጣትና ኃላፊነት" ባለመኖሩ እንደተፈፀመ አስታውቃለች።
"እስራኤል መጀመሪያ በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ከዛም ወደ አጎራባች ሀገራት የተዛመተ የራሷን ደህንነት እና መረጋጋት ማረጋገጥ የሚል ሰበብ አዘል ፖሊሲ እየተከተለች ነው።"
ቱኒዚያ የእስራኤልን "አምባገነናዊ እና ጠበኛ ባህሪ" ለማስቆም "ጠንካራ ጣልቃ ገብነት" እንዲደረግ አሳስባለች።
"በኢራን ላይ የተሰነዘረው አረመኔያዊ ጥቃት የእስራኤል ተደጋጋሚ እና የቀጠሉ ወንጀሎች እና ጥቃቶች አዲስ ምዕራፍና ሀገሪቱ በእብሪት እና ጠበኛ ፖለቲካዋ ላይ ያላትን ግትርነት ይበልጥ ያሳየ ነው።"
ሱዳን የእስራኤልን "ኢፍትሃዊ ጥቃት" "ለዓለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነት ከባድ ስጋት" ስትል ገልጻዋለች።
"ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት እና የፀጥታው ምክር ቤት እነዚህን ጥቃቶች በፍጥነት ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ታቀርባለች።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X