ሞስኮ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጉዳይ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ
18:31 14.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 14.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሞስኮ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጉዳይ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ
ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢራን አቻቸው አባስ አራግቺ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▫ሞስኮ እስራኤል በቴህራን ላይ የፈፀመችውን ወታደራዊ እርምጃ ታወግዛለች ሲሉ ላቭሮቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።
▫ሩሲያ በኢራን እና እስራኤል መካከል ያለውን ግጭት ለማርገብ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነች።
▫ላቭሮቭ እስራኤል በኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ለተጎዱት ሰዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
▫የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X