የኢራን እና በእስራኤል ግጭት አሁናዊ መረጃዎች፦

የኢራን እና በእስራኤል ግጭት አሁናዊ መረጃዎች፦
የደረሱ ጉዳቶች፦
▫ኢራን፡ 78 ሰዎች ሲገደሉ 320 ሰዎች ቆስለዋል።
▫እስራኤል፡ ቢያንስ 3 ሰዎች ሲሞቱ 91 ሰዎች ቆስለዋል
የኢራን የኒውክሌር ተቋማትና ሠራተኞች፦
▫እስራኤል 9 የኢራን የኒውክሌር ባለሙያዎችን ገድላለች።
▫ጥቃቶቹ በፎርዶውና ኢስፋሃን የኒውክሌር ጣቢያዎች ውስን ጉዳት አድርሰዋል።
የኢራን መልሶ መጥቃት እርምጃዎች፦
▫ኢራን በ4 ዙር ከ200 በላይ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች።
▫የእስራኤል ጦር ዋና መሥሪያ ቤት ተመቷል።
▫ኢራን የእስራኤል ጦር ዕዝና የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት ስርዓቶችን መትታለች።
▫25% የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤል የአየር መቃወሚያን አልፈዋል።
የቀጠሉ የእስራኤል ኦፕሬሽኖች፦
▫ በታብሪዝ የነዳጅ ማጣሪያዎች ፍንዳታዎች ተሠምተዋል።
▫ጥቃቱ በተለያዩ ሥፍራዎች የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን መቷል።
▫አራት የእስራኤል ድሮኖች ኮራማባድ አቅራቢያ ተመትተዋል።
▫በዛንጃን 3 የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት ተገድለዋል።
▫በምዕራብ ኢራን የማሽነሪ ፋብሪካ ተመቷል።
▫የኢራን አየር ክልል እሁድ ድረስ ተዘግቶ ይቆያል።
ይፋዊ መግለጫዎች እና ማስፈራሪያዎች፦
▫በተመድ የኢራን ልዑክ የእስራኤልን ድርጊት “መንግሥታዊ ሽብርተኝነት” ብለውታል።
▫ቴህራን አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ለእስራኤል ድጋፍ ከሠጡ ቀጣናዊ ንብረቶቻቸው ኢላማ እንደሚሆኑ አስጠንቅቃለች።
▫የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጥቃቶች “ለቀናት ወይም ለሳምንታት” ሊቆዩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
▫የመከላከያ ሚኒስትር ኢራን ጥቃቶቿን ከቀጠለች እስራኤል “ቴህራንን እንደምታቃጥል” አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X