ትራምፕ ኢራን ላይ በተካሄደው የጦርነት ድርጊት ተባባሪ ናቸው ሲል አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ታከር ካርልሰን ተናገረ
11:38 14.06.2025 (የተሻሻለ: 11:54 14.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ ኢራን ላይ በተካሄደው የጦርነት ድርጊት ተባባሪ ናቸው ሲል አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ታከር ካርልሰን ተናገረ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ኢራን ላይ በተካሄደው የጦርነት ድርጊት ተባባሪ ናቸው ሲል አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ታከር ካርልሰን ተናገረ
ፕሬዝዳንቱ እስራኤል በቴህራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት ከኢራን ጋር እየተካሄደ ላለው የኒውክሌር ንግግር እንደሚረዳ ተስፋ ያደርጋሉ ሲል በማለዳ የሚዲያ ሪፖርቱ አብራርቷል።
አሁን ላይ ቀጣዩ ዙር የአሜሪካ - ኢራን ንግግር መካሄዱ አጠራጣሪ እንደሆነም ጠቁሟል።
ካርልሰን "የአሜሪካ ጦር ጥቃቱን በተግባር ባይፈጽምም ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ በኩራት እንደተናገሩት፤ ለዓመታት ለእስራኤል የተደረገው የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ እገዛ አሜሪካ ትናንትና ማታ ለተከሰቱት ክስተቶች ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል" ብሏል።
ትራምፕ ስለ ጥቃቶቹ አስቀድመው እንደሚያውቁ አምነዋል ሲል ጋዜጠኛው አስረግጧል።
ሆኖም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዩ አሜሪካ እስራኤል ኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት እንዳልተሳተፈች ገልጸው፤ ዋሽንግተን ስለ ጥቃቶቹ ከእስራኤል መረጃ እንደደረሳት አስታውቀዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X