ፑቲን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከኢራን ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋገሩ
20:55 13.06.2025 (የተሻሻለ: 21:04 13.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከኢራን ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋገሩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን ጋር በስልክ መወያየታቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
በተጨማሪም ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ቀደም ብለው እንደተነጋገሩ ተገልጿል።
ፑቲን ሁለቱን መሪዎች በስልክ ማነጋገራቸውን ተከትሎ በክሬምሊን የተሰጡ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
▪ ፑቲን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር እና ዓለም አቀፍ ሕግ የጣሰውን የእስራኤል ድርጊት ሩሲያ ታወግዛለች ብለዋል።
▪ ፑቲን በእስራኤል ጥቃት ሳቢያ ለደረሠው በርካታ ሞት ለኢራን መንግሥት እና ሕዝብ ሐዘናቸውን ገልፀዋል።
▪ ሩሲያ በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ የበኩሏን አስተዋጽኦ ማድረግ ትቀጥላለች።
▪ ሩሲያ የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሚደረገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ ትደግፋለች።
▪ ፑቲን ከኔታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት ወደ ድርድር ሂደት የመመለስን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።
▪ ፑቲን ውጥረቱ እንዳይባባስ ለማሸጋመል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
▪ የኢራን ፕሬዝዳንት ቴህራን ለእስራኤል ጥቃት ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ለፑቲን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X