እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት - የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደ 'ኮሊን ፓውል’ ለሕገ-ወጥ ተግባር አመክንዮ ለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው ጠቆሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት - የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደ 'ኮሊን ፓውል’ ለሕገ-ወጥ ተግባር አመክንዮ ለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው ጠቆሙ
እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት - የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደ 'ኮሊን ፓውል’ ለሕገ-ወጥ ተግባር አመክንዮ ለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው ጠቆሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.06.2025
ሰብስክራይብ

እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት - የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደ 'ኮሊን ፓውል’ ለሕገ-ወጥ ተግባር አመክንዮ ለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው ጠቆሙ

የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ  በዚህ የጂኦፖለቲካል ቴአትር ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ሲሉ ቬንዚዌላዊው የጂኦፖለቲካል ኤክስፐርት ኦስዋልዶ ኢስፒኖዛ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን በተመለከተ በቂ ግልጸኝነት እንዳላሳየች እና ኒውክሌር እያበለጸገች ያለችውም ለወታደራዊ ዓላማ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል...ይህም አሜሪካ በኢራቅ ላይ የፈጸመችውን ወረራ ለማስረዳት ኮሊን ፓውል ከታዋቂዋ የናሙና መውሰጃ ብልቃጥ ጋር የነበራቸውን ሚና የሚያስታውስ ነው" ብለዋል።

ኤክስፐርቱ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እ.አ.አ በ2003 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፤ ኢራቅ አላት  ያሉትን ሐሰተኛ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አደገኛነት ለማስረዳት "የአባ ሰንጋ" በሽታ ናሙና በብልቃጥ ይዘው ነበር።

ለኤስፒኖዛ "ይህ የጦርነት ድርጊት ለመሆኑ እና የምዕራቡ ዓለም ሁልጊዜ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ለሁኔታው አመቺ ዓውድ እንደሚፈጥር" አያወላዳም።

"የኢራን ወሳኝ የአጸፋ ምላሽ ብዙ ጊዜ አይወስድም፤ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል በምትፈጽማቸው ጥቃቶች ላይ ያላትን ተሳትፎ ብታስተባብልም፤ የጥቃት ኢላማዎችን ለመለየት እና በትክክል ለመምታት የአሜሪካ የደኅንነት አቅም ያስፈልግ አንደነበረም ግልጽ ነው" ሲሉም አብራርተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0