“ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከውጭ ኤክስፐርቶች ጥገኝነት ለመላቀቅ የሩሲያን የትምህርት ስርዓት እንደ አማራጭ ትመለከታለች”

ሰብስክራይብ

“ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከውጭ ኤክስፐርቶች ጥገኝነት ለመላቀቅ የሩሲያን የትምህርት ስርዓት እንደ አማራጭ ትመለከታለች”

"ቁንጮ ትምህርት ቤቶች እና የስልጠና መስኮች ያስፈልጉናል። ለዚህም ነው ሩሲያ ውስጥ ያለውን የትምህርት መዋቅር ዓይነት በእኛም ሀገር ለመዘርጋት ከሩሲያ ጋር አየሠራን ያለነው" ሲሉ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ሎረን ሲሳ ማጋሌ ተናግረዋል።

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ "ባህሪን በኃይል ከሚቀርጹ" ኤክስፐርቶች ተላቅቃ፤ የምትፈልገውን በራሷ መበየን እንደሚገባትም ሚኒስትሩ በሩሲያ ካዛን እየተካሄደ ካለው ዓለም አቀፉ የትምህርት ሚኒስትሮች ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ሀገሪቱ የውጭ ተፅዕኖዎችን ለመመከት የትምህርት "ምሰሶዎችን ልትገነባ እንደሚገባ እና ይህን ግብም ለማሳካት በአግባቡ የተደራጀውን የሩሲያን የትምህርት ሥርዓት መመልከት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

"ሀገራችን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እየተመለሰች ነው፤ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ ናቸው። ዩኒቨርሲቲዎችም ወደ መደበኛ መማር ማስተማር እየገቡ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ አክለውም ሩሲያ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት የምታደርገው ድጋፍ የትምህርት ዘርፉን እያገዘ መሆኑን አመላክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0