ሩሲያ ለሴኔጋል ትምህርት መነሳሳት አርዓያ መሆን ትችላለች ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለሴኔጋል ትምህርት መነሳሳት አርዓያ መሆን ትችላለች ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ

የሴኔጋል የትምህርት ሚኒስትር ሙስታፋ ማምባ ጉራሲ ሩሲያ ለአፍሪካውያን ቅርብ የሆኑትን የቤተሰብ እሴቶች፣ ባሕል እና ተፈጥሮን ትጠብቃለች ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት በተለያዩ አቅጣጫዎች ላይ ቢሆኑም "ተመሳሳይ እሴቶችን ይሻሉ” ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከሩሲያ የምወስደው ከባሕል፣ ወግ፣ ሉዓላዊነት እንዲሁም ክብር ጋር ያላትን ቁርኝት ነው" ብለዋል።

በሩሲያ ካዛን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የትምህርት ሚኒስትሮች መድረክ ላይ የሚገኙት ሙስታፋ ማምባ ጉራሲ፤ ከተማዋ የሰላማዊ መስተጋብር መገለጫ እንደሆነች በአጽዕኖት ተናግረዋል።

"50% የሚጠጋው ሙስሊም እና 50% ክርስቲያን ሕዝብ ነው ያለው። ይህ የሚያሳየው አብረን መኖር እንደምንችል ነው፤ የጋራ መከባበር ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነገር ነው። የሰላም ባሕል ለመፍጠር እነዚህ መርሆዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ መስረጽ አለባቸው" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0