ኢትዮጵያ የእርሻ ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ የመንግሥት አካል ማቋቋሟን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የእርሻ ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ የመንግሥት አካል ማቋቋሟን አስታወቀች
ኢትዮጵያ የእርሻ ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ የመንግሥት አካል ማቋቋሟን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.06.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የእርሻ ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ የመንግሥት አካል ማቋቋሟን አስታወቀች

በግብርና ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው እና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና በጃፓን አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ አዲስ ክፍል፤ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ በአነስተኛ ማሳ ለሚያመርቱ አርሶና አርብቶ አደሮች የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነትን የሚገድቡ ስርዓታዊ የገበያ እንቅፋቶችን ለመፍታት ያለመ ነው።

የገጠር ፋይናንስ ክፍል ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና አለው ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ  "የኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ የገጠር ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ ገበያዎችን በመገንባት ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ነው" ሲሉ በአነስተኛ ማሳ ለሚያመርቱ አርሶና አርብቶ አደሮች የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ላይ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0