የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በብሪክስ የማዘጋጃ ቤቶች መድረክ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበለት
19:46 11.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 11.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በብሪክስ የማዘጋጃ ቤቶች መድረክ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበለት
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሞስኮ ከተማ ምክር ቤት (ዱማ) ሰብሳቢ አሌክሲ ሻፖሽኒኮቭ ጋር በሞስኮ እና አዲስ አበባ የጋራ ትብብር መስኮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሻፖሽኒኮቭ በብሪክስ ሀገራት ዋና ከተሞች መካከል የፓርላማ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የሞስኮ ከተማ ዱማ የጀመረውን ተነሳሽነት በተመለከተ ገለጻ እንዳደረጉ ሩሲያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕግ አውጭዎች ሞስኮን እንዲጎበኙ እና በመጪው ጥቅምት በሴንት ፒተርስበርግ በሚካሄደው የብሪክስ ማዘጋጃ ቤት መድረክ ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።
አምባሳደር ገነት ኢትዮጵያ ሩሲያ ለምትመራው የፓርላማ እንቅስቃሴ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ አስተዳደር እንቅሰቃሴውን ለመቀላቀል እንደወሰነ አንስተዋል።
አምባሳደሩ የሞስኮ ዱማ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝት የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የከተማ ፕሮጀክቶችን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X