#SovereigntySources | ሠው ሰራሽ አስተውህሎት፡የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት አዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ

ሰብስክራይብ

#SovereigntySources | ሠው ሰራሽ አስተውህሎት፡የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት አዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን በማሻሻል እየሰራች ነው ።

ለዚህም ከሩሲያ ጋር ትብብርን በመፍጠር ማርሽ ቀያሪ  አጋርነትን መሥርታለች። ትብብሩ ከሮቦቲክስ እስከ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ድረስ በደቡባዊው ዓለም ውስጥ ፈጠራን እንደ አዲስ  ያስተዋውቃል።

የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችንም በጉዳዩ ላይ  የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ  ባህሩ አባስን ወደ ስፑትኒክ ስቱዲዮ ጋብዞታል ።

የባለሙያው ዕይታ

“ይህ የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ አይደለም -  የሉዓላዊነት ጉዳይም እንጂ። ኢትዮጵያ የሠው ሰራሽ አስተውሎት አቅሞቿን ወደ ላቀ ደረጃ ማስፈንጠር ትችላለች፣ ሩሲያም በአፍሪካ የዲጂታል ምጣኔ ሐብት ላይ ያላትን ተሳትፎ ታረጋግጣለች” ሲል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው  ባህሩ አባስ ተናግሯል።

ከጂኦ ፖለቲካ ባሻገር፡ በኢትዮጵያ በሠው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ማዕቀፍ ፣ የሩሲያ  እና  ብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን  መሠረት ያደረገ አጋርነት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ተራማጅ ዘርፍ እንዲገነቡ ያነሳሳቸዋል።

በሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕርግራም የሚቀርበውን ሙሉ መሠናዶ ለመከታተል ዝግጁ ነዎት?

ይህን ይጫኑ እና ከቴሌግራም ሳይወጡ በ ከፍተኛ የድምፅ ጥራት መረጃውን ያድምጡ።

ከቴሌግራም ቻናላችን በተጫማሪም ፕሮግራሞቻችን በ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ድረ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0