ኢትዮጵያ በ2025 ግዙፍ አምራች ኩባንያዎች መገኛ ከሆኑ 10 የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተቀመጠች
17:11 11.06.2025 (የተሻሻለ: 17:54 11.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2025 ግዙፍ አምራች ኩባንያዎች መገኛ ከሆኑ 10 የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተቀመጠች
በአፍሪካ የንግድ ተቋማትና ባለሃብቶች ዙሪያ ትንተናዊ መረጃዎችን የሚያቀርበው ዘ አፍሪካን ኤክስፖነት ባደረገው ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አስር ቀዳሚ አምራች ሀገራት መካከል ሰባተኛ ደረጃን አግኝታለች።
ለውጤቱ በምክንያትነት የቀረቡ ምክንያቶች፦
🟠የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች፣
🟠ርካሽ የሰው ኃይል፣
🟠ወጪ ንግድ ላይ የተመሠረት የአምራች ኢንዱስትሪ እድገት፡፡
ሀገሪቱ በተለይም ለጨርቃ ጨርቅ፣ ሲሚንቶ እና የምግብ ማቀነባበሪያ አምራቾች ማራኪ እንደሆነች ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
አፍሪካ ውስጥ ትላልቅ አምራች ኩባንያዎች የሚገኙባቸው 10 ቀዳሚ ሀገራት—ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ኬንያ፣ አልጄሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ቱኒዚያ እና ዛምቢያ በመሆን ተቀምጠዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X