በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አምስት ከተሞች ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸው ተነገረ
14:09 11.06.2025 (የተሻሻለ: 14:34 11.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አምስት ከተሞች ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸው ተነገረ
ዳራቶሌ፣ ሂግሉሌ፣ ቦቆማልዮ ከተማን ጨምሮ በሌሎች ሁለት ከተሞች የሚኖሩ ከ144 ሺህ በላይ ሰዎች ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።
በአገልግሎቱ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ማዕከሎች፣ የንግድ ተቋማት እና የአስተዳደር ቢሮዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታውቋል።
በአገልግሎቱ ሰባት ሺህ ቤቶች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን በቀጣይ ከ36 ሺህ በላይ ቤቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X