የኢትዮጵያና ሩሲያ የንግድ ልውውጥ በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት 40 በመቶ አሻቀበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያና ሩሲያ የንግድ ልውውጥ በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት 40 በመቶ አሻቀበ
የኢትዮጵያና ሩሲያ የንግድ ልውውጥ በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት 40 በመቶ አሻቀበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.06.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያና ሩሲያ የንግድ ልውውጥ በፈረንጆቹ 2024 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት 40 በመቶ አሻቀበ

የሩሲያ ላኪዎችና አስመጪዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሪና ዛሴዳቴል "በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው የንግድና ኢኮኖሚያዊ ትብብር በሁለትዮሽ እና በብሪክስ ደረጃ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ መጥቷል" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

በድርቅ አያያዝ እና የስንዴ ዝርያዎችን በማዳቀል ረገድ የሩሲያ ልምድ ለኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና እንደሚጠቅም ሊቀመንበሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብርና ከፍተኛ የንግድ ልውውጥን የሚያንቀሳቅስ ትልቅ ዘርፍ ነው ብለዋል።

ከግብርና በተጨማሪ የሁለቱ ሀገራት የጋራ ፍላጎት ዘርፎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች፣

🟠ኬሚስትሪ፣

🟠ፋርማሱቲካል፣

🟠መሠረተ ልማት ግንባታ፣

🟠ትራንስፖርት፣

🟠የኤሌክትሪክ ኃይል፣

🟠ሰላማዊ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎች፡፡

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን እንዲያሳድጉ በሎጂስቲክስ፣ በፈቃድ አሰጣጥ እና በንግድ ግንኙነት ዙሪያ ያሉ ማነቆዎችን መፍታት አለባቸው ሲሉ ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

እነዚህ ችግሮች ከተፈቱ ኢትዮጵያ ገበያ እና ቴክኖሎጂ ማግኘት እንደምትቸል፤ ሩሲያ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ ታማኝ አጋር እንደሚኖራት ገለፀዋል። ይህ ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና የብሪክስን የምዕራባውያን የበላይነት እውነተኛ ተቀናቃኝነት እንደሚያጠናክር አስረድተዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0