"የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ይበልጥ ሊተባበሩ ይገባል"
21:54 10.06.2025 (የተሻሻለ: 22:04 10.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ይበልጥ ሊተባበሩ ይገባል"

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ይበልጥ ሊተባበሩ ይገባል"
የአፍሪካ የደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ኅብረት ተወካይ ፖል-ሲሞን ሃንዲ፤ ከዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎች ቀን ጎን ለጎን የተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ትኩረት ያድርጉባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች ለስፑትኒክ አፍሪካ አጋርተዋል።
"በተልዕኮዎች ውስጥ ከወታደሮች እና ፖሊሶች ባሻገር በሰብዓዊ ዕርዳታ፣ በመልሶ ግንባታ እና በማኅበራዊ አገልግሎት ላይ የሚሳተፉ ሲቪሎች ለዘላቂ ሰላም ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው። ሁለገብ የሰላም ማስከበር ስልት ለዘላቂ ሰላም እና ልማት ባለው አበርክቶ ላይ የጋራ መረዳት አየተፈጠረ ይመስለኛል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህን ሐሳብ በአፍሪካ ኅብረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተቋማዊ እና ኦፕሬሽናል አጋርነት አገልግሎት ኃላፊ ሄስተር ፓናራስ ይጋሩታል።
በተልዕኮዎች ውስጥ የሚሳተፉ ሲቪል ሙያተኞች በጦርነት የተዳከሙ እና የተቋረጡ አገልግሎቶች ዳግም እንዲነቃቁ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዙ አጽዕኖት ይሰጣሉ።
"ተልዕኮዎች ከሠራዊት ባለፈ ለዘላቂ ሰላም ምን ዓይነት አዳዲስ አቀራረቦችን እና ቴክኖሎጂዎችን ቢከተሉ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናሉ የሚለውን በጥልቀት መፈተሽ ያስፈልጋል" ሲሉም በአበክሮ ተናግረዋል፡፡
🪖 ኃላፊዎቹ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ መልካም ስም ያላት ሀገር መሆኗን በማውሳትም ሀገሪቱ ስለ አፍሪካ እና ስለ ዓለም ሰላም ዋጋ መክፈሏን አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X