“የኃይል ልማት የኢትዮ-ሩሲያ ቁልፍ የትብብር መስክ ሊሆን ይገባል” የውኃ ሐብት ባለሙያው ፈቅአሕመድ ነጋሽ

“የኃይል ልማት የኢትዮ-ሩሲያ ቁልፍ የትብብር መስክ ሊሆን ይገባል” የውኃ ሐብት ባለሙያው ፈቅአሕመድ ነጋሽ
ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የውኃ ኃብቷ ውስጥ እስካሁን ለኃይል ምንጭነት የተጠቀመችው ከ10 በመቶ፣ ለመስኖ ደግሞ ከ3 በመቶ እንደማይበልጥ የድንበር ተሻጋሪ ውኃ ሐብት ባለሙያና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀድሞ ተደራዳሪ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገረዋል።
"ሀገሪቱ ከውኃ ኃይል ምንጭ ባሻገር በንፋስ፣ በአየር፣ በጸሐይ እና በሌሎች ታዳሽ የኃይል ምንጮች ያላት እምቅ አቅም፤ በዘርፉ የዳበረ ልምድ ካላት ሩሲያ ጋር ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለመፍጠር ያስችላል" ብለዋል።
መልካ ዋከና የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ እ.አ.አ በ1988 በሩሲያ እና ሀንጋሪ ባለሙያዎች መገንባቱን ያስታወሱት ፈቅአሕመድ ነጋሽ፤ ሶቪየት ሕብረት በወቅቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር ለተለያዩ ወዳጅ ሀገራት ግዙፍ የኃይል ማመንጫዎችን መገንባቷን አውስተዋል። ኢትዮጵያ፤ ሩሲያ በዘርፉ ካላት የረጅም ዘመናት የካበተ ልምድ የዕውቀት ሽግግር ማድረግ ብትችል፤ የሩሲያ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ የኃይል ምንጭ ልማት ላይ በንቃት ቢሳተፉ፤ የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ፋይዳ እንደሚኖረው አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በያሉበት አሕጉር የበርካታ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች መነሻ እንደመሆናቸው መጠን በውኃ ሐብት አጠቃቀም ላይ ሰፊ የልምድ ልውውጥ ሊያደርጉ አንደሚችሉም ጠቁመዋል።
"ሩሲያ አንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የላይኛው ተፋሰስ ሀገር ናት። የውኃ ሐብትን በፍትሐዊነት መጠቀም ላይ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች ላይ ተሞክሮዎችን ከመለዋወጥ ባለፈ በፖሊሲ ጭምር ሊተባበሩ ይችላሉ"
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ባሻገር በተለይ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ ከሚገኙ እና በግድብ ግንባታ እና በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ የረጅም ዘመናት ልምድ ካላቸው እንደ ቻይና አና ብራዚል ካሉ ሀገራት ጋር በዘርፉ ያላትን ግንኙነት ማጠናከር አንደሚገባትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X