ኢትዮጵያ በ2022 የአፍላ ወጣቶችን እርግዝና ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ አዘጋጀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2022 የአፍላ ወጣቶችን እርግዝና ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ አዘጋጀች
ኢትዮጵያ በ2022 የአፍላ ወጣቶችን እርግዝና ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ አዘጋጀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.06.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2022 የአፍላ ወጣቶችን እርግዝና ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ አዘጋጀች

በኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታዳጊ ልጃገረዶች መካከል 16 በመቶ የሚሆኑት በወጣትነታቸው እንደሚያረግዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። መንግሥት ይህንን ቁጥር እስከ 2022 ዓ.ም ወደ 3 በመቶ ዝቅ የማድረግ ግብ አስቀምጧል።

"የአፍላ ወጣትነት እርግዝና የጤና ጉዳይ ብቻ አይደለም። ከባድ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዘዞች አሉት" ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ደኤታ ደረጀ ዱጉማ መናገራቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

አክለውም ወጣቶችን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶችን ማስፋፋት እና በሚገባ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎችን መመደብ የፍኖተ ካርታው ዋና አካላት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0