ኢራን በእስራኤል ላይ የመረጃ ድል እንደተቀዳጀች ይፋ አደረገች
17:56 08.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 08.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢራን በእስራኤል ላይ የመረጃ ድል እንደተቀዳጀች ይፋ አደረገች
የኢራን የደህንነት ሚኒስቴር ያልተጠበቀ የስለላ መረጃ አውጥቷል!
የደህንነት ሚኒስትሩ እስማኤል ካቲብ በቅርቡ ኢራን ስላሳካችው እጅግ ከፍተኛ ኦፕሬሽን ለብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ከተናገሯቸው፦
▪በሺዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደራዊ፣ የኒውክሌር እና ሳይንሳዊ ዘርፍ ሰነዶች በኢራን እጅ ገብተዋል።
▪እስራኤል ከአሜሪካ እና ከምዕራባውያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ ወሳኝ መረጃም ተገኝቷል።
▪ሰነዶቹ የኢራንን የማጥቃት አቅም በእጅጉ የሚያሳዳጉ መጠነ ሰፊ አንደምታ ያላቸው ናቸው።
▪ፋይሎቹ በኢራን እጅ እንዴት ሊገቡ ቻሉ? በሚስጥር ተይዟል፤ ሚስጥር ሆኖም ይቀጥላል።
▪ይህ ውስብስብና ብዙ ገፅታ ያለው ኦፕሬሽን ለእስራኤል የደህንነት መረብ ከፍተኛ ጉዳት አለው።
▪አንዳንድ ሰነዶች በቅርቡ ይፋ ይሆናሉ።
ሚዛኑን ያናዋጠ ግዙፍ የመረጃ ኦፕሬሽን። ግኝቱ በኢራን እጅ ገብቷል፤ ይህም ገና ጅምር ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X