ኢትዮጵያ ወደ ህንድ የምትልከውን የማዕድን ምርት እንድታሳድግ ተጠየቀ
17:36 08.06.2025 (የተሻሻለ: 17:54 08.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ወደ ህንድ የምትልከውን የማዕድን ምርት እንድታሳድግ ተጠየቀ
ኢትዮጵያ እና ህንድ የማዕድን ወጪ ንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን የተመለከተ ፍኖተ ካርታ ይፋ አድርገዋል።
ሁለቱ ሀገራት የጎለበተ የንግድ ግኑኝነት ቢኖራቸውም በማዕድን ዘርፍ ያለውን አቅም መጠቀም በተመለከተ ገና መሆናቸውን የማዕድን ሚኒስትር ደኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ጥሬ እቃ ብቻ ሳይሆን እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ለመላክ ሂደቶችን እያመቻቸች እንደሆነ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጿል።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በበኩላቸው ኒው ዴልሂ የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በኢንቨስትመንት፣ በአቅም ግንባታ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለመደገፍ ዝግጁ ናት ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X