የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካን የጭነት ገበያ 35 በመቶ ተቆጣጥሯል ሲል አስታወቀ
16:45 08.06.2025 (የተሻሻለ: 19:24 08.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካን የጭነት ገበያ 35 በመቶ ተቆጣጥሯል ሲል አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካን የጭነት ገበያ 35 በመቶ ተቆጣጥሯል ሲል አስታወቀ
ተቋሙ የአህጉሪቱን ዓመታዊ የመሠረተ ልማት ሪፖርት ይፋ ሲያደርግ የገለፀው እንደሆነ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።
የኢትዮጵያን አየር መንገድ አስመልክቶ በሪፖርቱ የተነሡ ዋና ዋና ሀሳቦች፦
▪አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2016 የነበረውን 266 ሺህ ቶን የጭነት ማጓጓዝ አቅም በ2023 ወደ 715 ሺህ ቶን አሳድጓል።
▪ከአየር መንገዱ 60 ዓለም አቀፍ የጭነት መዳረሻዎች ግማሹ በአፍሪካ ይገኛሉ።
▪አየር መንገዱ 16 የጭነት አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን በ2035 ቁጥራቸውን ወደ 37 ለማሳደግ አቅዷል።
በሌላ በኩል ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት መጠን ቀዳሚ እንደሆነች ገልጿል።
🟠 የኢትዮጵያ የስንዴ ዘር ሽፋን በ2018 ከነበረበት 5 ሺህ ሄክታር በ2023 650 ሺህ ሄክታር አልፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X