ኢትዮጵያ የህክምና ጓንትና ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት አቆመች
14:11 08.06.2025 (የተሻሻለ: 14:34 08.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የህክምና ጓንትና ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት አቆመች
በሀገሪቱ የሚገኙ ሁለት የጓንት አምራቾች የኢትዮጵያን ጠቅላላ የጓንት ፎጆታ በመሸፈን ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
በሌላ በኩል በድሬዳዋ የሚገኘው የስሪንጅ ፋብሪካ ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ ምርቶቹን ለኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እያቀረበ እንደሚገኝ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ ምርት ያለበት ሁኔታ፦
🟠 የአምራቾች አቅርቦት ድርሻ በሦስት ዓመት ውስጥ ከ8% ወደ 37% አድጓል።
🟠 ኢትዮጵያ 60% መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት አቅዳ እየሠራች እንደሆነም ተገልጿል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X