ኢትዮጵያ በክሪፕቶ ግብይቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ልትጀምር ነው
13:47 08.06.2025 (የተሻሻለ: 14:04 08.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በክሪፕቶ ግብይቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ልትጀምር ነው
ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በቨርችዋል ግብይት ላይ ክልከላ ብታስቀምጥም አስፈላጊውን የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፍ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ የፋይናንስ መረጃ አገልግሎት አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ኃላፊ ሙሉቀን አማረ "ከኢትዮጵያ ብር ወጪ በቨርቹዋል መገበያያ ልውውጥ ማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ ክልክል ነው፤ ላልተፈቀደ ንግድ ለመዘጋጀት ስልጠና እየሰጠን ነው" ሲሉ በቅርቡ በተካሄደው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን መከላከል ስብሰባ ላይ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ ተናግረዋል።
ግልፅ የቁጥጥር ማዕቀፍ መኖር እንዳለበት አጽንኦት የሰጡት ኃላፊው፤ "የክሪፕቶ ግብይት "
ወደፊት ሕጋዊ የሚሆን ከሆነ" ተገቢ ቁጥጥር ሊኖር እንደሚገባና "ክልከላው የሚቀጥል ከሆነ ሕግ ለማስከበር እና አጥፊዎችን ለመቅጣት የሚያስችል ስርዓት ሊኖር ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X