የኢራን እና ሩሲያ የሕዋ ትብብር መጥቋል ተበላ
16:04 07.06.2025 (የተሻሻለ: 16:24 07.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢራን እና ሩሲያ የሕዋ ትብብር መጥቋል ተበላ
የኢራን አምባሳደር ካዜም ጃላሊ እና የሮስኮስሞስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሚትሪ ባካኖቭ የጋራ ሳተላይቶች ምርት እና የላቁ ቴክኖሎጂዎች ልማትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በሞስኮ ተወያይተዋል።
እንደ ኢራን ኤምባሲ ገለጻ ውይይቱ፦
▫የስልጠና ፕሮግራሞችን እና የእውቀት ልውውጥን ማካሄድን፤
▫ የምዕራባውያንን ማዕቀቦች መቋቋምና
▫ዓለም አቀፍ ሰላምን እና መረጋጋትን ለማጠናከር የሚደረጉ የጋራ ጥረቶችን መደገፍን ያካተተ ነበር።
ባለፈው ህዳር መጀመሪያ ላይ የሩሲያ ሶዩዝ-2.1ቢ ሮኬት የኢራንን የኮውሳር ምድር ምልከታ ሳተላይት እና የሆድሆድ የቴሌኮሙኒኬሽን ሳተላይትን ጨምሮ 53 ትናንሽ የጠፈር መንኮራኩሮችን በተሳካ ሁኔታ ማስወንጨፉ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X