የአዲስ አበባ የደን ሽፋን 20 በመቶ መድረሱ ተገለፀ
16:56 06.06.2025 (የተሻሻለ: 17:04 06.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ የደን ሽፋን 20 በመቶ መድረሱ ተገለፀ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ፅዱ ኢትዮጵያን መፍጠር" በሚል መሪ ቃል የተከበረውን የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የከተማው የደን ሽፋን 2 ነጥብ 8 መቶ እንደነበር አስታውሰዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
አክለውም አስተዳደራቸው በዘላቂ የከተማ ልማት፣ አረንጓዴ ቦታዎችን በማስፋፋት፣ በኮሪደር እና በየወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክቶች መዲናዋን እያስዋበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ፦
🟠160 የሕዝብ መናፈሻዎችን፤
🟠 ከ2 ሺህ በላይ የህፃናት መጫወቻ ሥፍራዎችንና
🟠 454 የንፅህና መጠበቂያ በታዎችን በመገንባት በአዲስ አበባ የአረንጓዴ ተነሳሽነቶችን እየተገበረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ትራንስፖርቶችን በተመለከተ፦
🟠 100 የኤሌክትሪክ አወቶብሶችን፣
🟠 150 አነስተኛ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን እና
🟠 ለሞተር አልባ እንቅስቃሴ 244 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ መገንባቱን ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X