የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ3 ቢሊየን ዶላር ተሻገረ
16:11 06.06.2025 (የተሻሻለ: 16:34 06.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ከ3 ቢሊየን ዶላር ተሻገረ
ይህ የተገለፀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤተ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በግብርና ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።
በግምገማው ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ከ400 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ ተልኮ 2 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል።
▪ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች፣ ቅመማ ቅመሞች፣ የቁም እንስሳት እና የእንስሳት ተዋፅኦዎች ገቢ ከተገኘባቸው የግብርና ምርቶች ውስጥ ይካተታሉ።
▪ 31 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለእርሻ ዝግጁ የተደረገ ሲሆን በያዝነው ዓመት 7 ሚሊየን ሄክታር አዲስ የእርሻ መሬት ማካተት ተችሏል።
▪ በአረንጓዴ አሻራ የደን ልማት ከ7 ቢሊየን በላይ ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን 500 ሚሊየን የሚሆኑት ቀድመው ተተክለዋል።
▪ ለመጪው የግብርና ወቅት 24 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ተገዝቷል፤ ከዚህ ውስጥ 12 ሚሊየን ኩንታል አስቀድሞ ለክልሎች ተሰራጭቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X