ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሁለት ድልድዮችን ሊገነቡ ነው
12:58 06.06.2025 (የተሻሻለ: 13:04 06.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሁለት ድልድዮችን ሊገነቡ ነው
ሁለቱ ሀገራት በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አስተባባሪነት በአፍሪካ ቀንድ የሁለትዮሽ ትብብር ልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ትናንት በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል።
አዲስ አበባ እና ናይሮቢ በዳዋ ወንዝ ላይ ሁለት ድልድዮችን ለመገንባት እንደተስማሙ ኢጋድ በመግለጫው አስታውቋል።
ድልድዮቹን "የተስፋ መተላለፊያዎች" ሲል የገለፀው ኢጋድ፤ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን በቂ የመሠረታዊ አገልግሎቶች የማያገኙ ማሕበረሰቦችን ምኞት የሚስተላልፍ ነው ብሏል።
በተጨማሪም የራሙ አንድ አለቅ የድንበር ጣቢያ እና የሱፍቱ የንግድ ማሳለጫ ማዕከል ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገልጿል።
ሀገራቱ የድንበር ተሻጋሪ የፋይበር ኦፕቲክ ግንኙነትን ለማጠናቀቅ፣ የድንበር ተሻጋሪ ዲጂታል አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X