የናይጄሪያ መንግሥት በጎርፍ አደጋ ከ200 በላይ ሰዎች ለሞቱባት የሞክዋ ከተማ ነዋሪዎች የ1.3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ሰብስክራይብ

የናይጄሪያ መንግሥት በጎርፍ አደጋ ከ200 በላይ ሰዎች ለሞቱባት የሞክዋ ከተማ ነዋሪዎች የ1.3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የሀገሪቱ መንግሥት ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከገንዘብ ድጋፉ ባሻገር 20 እህል የጫኑ መኪናዎችን ልኳል።

"የደረሰው አደጋ አሰቃቂ ቢሆንም የእናንተን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ግን ሊበይን አይገባም። ሞክዋ ከተማ የምትታወቅበትን የደመቀ መልክ መልሰን እንገነባለን" ሲሉ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ በምዕራብ ናይጄሪያ በምትገኘው የኒጀር ግዛት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል።

በአደጋው እስካሁን 100 የሚደርሱ ሰዎች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን የሀገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲም ተጎጂዎችን የመፈለጉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

እንደ ኤጀንሲው መረጃ የጎርፍ አደጋው ያደረሳቸው የተረጋገጡ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

▪ቢያንስ 11 ሰዎች ቆስለዋል፣

▪ከ265 በላይ ቤቶች ወድመዋል፣

▪በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፣

▪ወሳኝ በሆነው የሞክዋ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በሞክዋ ከተማ ጉብኝት ሲያደርጉ የሚያሳይ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0