በናይጄሪያ የሚመረቱ ወታደራዊ መሳሪያዎች እየጨመሩ ነው ሲሉ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
18:27 05.06.2025 (የተሻሻለ: 18:34 05.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበናይጄሪያ የሚመረቱ ወታደራዊ መሳሪያዎች እየጨመሩ ነው ሲሉ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ የሚመረቱ ወታደራዊ መሳሪያዎች እየጨመሩ ነው ሲሉ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
የመከላከያ ሚኒስትሩ መሐመድ ባዳሩ ይህም ናይጄሪያ በጦር መሳሪያ እራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት እያረጋገጠ ነው ብለዋል።
"በወታደራዊ መሳሪያዎች ስልጠና፣ የሀገር ውስጥ ምርት እና እድሳት ላይ እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች የሚደነቁ ናቸው" ሲሉ ሚኒስትሩ በሰሜናዊ ካዱና ግዛት የሚገኙ ቁልፍ ወታደራዊ ተቋማትን በጎበኙበት ወቅት ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉ የውጊያ መሳሪያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
▪ብረት ለበስ ወታደሮችን ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች፣
▪ፈንጂ የሚቋቋሙና የደፈጣ ጥቃት የሚከላከሉ ተሽከርካሪዎች፣
▪ጥይት የማያሳልፍ መስታወት፣
▪ መለዋወጫዎች፣
▪የስለላ ድሮኖች ።
አንዳንዶቹ መሳሪያዎች ወደ ውጊያ ቀጣናዎች ከወዲሁ መላካቸውን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ