በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በ951.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ተመረቀ
14:15 05.06.2025 (የተሻሻለ: 14:34 05.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በ951.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ተመረቀ
በደገሃቡር ከተማ የተገነባው ፕሮጀክት 134 ኪሎ ሜትር ዋና መስመር እና የማከፋፈያ ኔትወርኮች እንዳሉት ተገልጿል።
የውሃ አቅርቦት ስርዓቱ ለ20 ዓመታት እንዲያገለግል ሆኖ እንደተነደፈ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ዑመር አስታውቀዋል።
በክልሉ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት እ.ኤ.አ 2018 ከነበረው 20% አሁን ወደ 51% ከፍ ማለቱን ጨምረው ገልፀዋል።
ሽፋኑ የጨመረው 17 የከተማ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን፣ 46 የገጠር ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን፣ 340 ስትራቴጂካዊ የውሃ ጉድጓዶችን እና 15 ትናንሽና መካከለኛ ግደቦችን በመሥራት ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ