ፑቲን ኪዬቭ ድርድሩን ለማሰናከል ብትሞክርም ሞስኮ ቅስቀሳዎቹን ተቋቁማለች ሲሉ ለትራምፕ አስታወቁ

ፑቲን ኪዬቭ ድርድሩን ለማሰናከል ብትሞክርም ሞስኮ ቅስቀሳዎቹን ተቋቁማለች ሲሉ ለትራምፕ አስታወቁ
የሁለቱን መሪዎች የስልክ ውይይት ተከትሎ በፕሬዝዳንት ፑቲን ረዳት ኡሻኮቭ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
🟠 ፑቲን በኢስታንቡል በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተደረገው ድርድር ጠቃሚ እንደነበር አጽንኦት ሰጥተዋል።
🟠 የኪዬቭ አገዛዝ በመሠረታዊነት ወደ አሸባሪ ድርጅትነት መቀየሩን ገልጸዋል።
🟠 መሪዎቹ የዩክሬንን ግጭት መፍታት የሚያስችሉ ነጥቦች ላይ አልተወያዩም።
🟠 በፑቲን እና በዘለንስኪ መካከል የሚደረግ ግኑኝነት "አጀንዳ አልነበረም።"
🟠 ትራምፕ የሩሲያ የአየር ማረፊያዎች ላይ ስለደረሰው ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ ቀድማ እንደማታውቅ ገልጸዋል።
🟠 "ሩሲያ ከአሸባሪዎች ጋር ስለምታደርገው ድርድር"፦ ጉዳዩን ለመፍታት በተገቢ መስመሮች አማካኝነት ግንኙነቶች ሊደረጉ ይችላሉ።
🟠 ትራምፕ ሩሲያ ከኢራን ጋር በኒውክሌር ስምምነቱ ዙሪያ አብራ ብትሠራ ደስተኛ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
🟠 ፑቲን እና ትራምፕ እጅግ በጣም ሰፊ አቅም ያለውን የሁለቱን ሀገራት ትብብር የመመለስ ተስፋዎች ላይ የጋራ አስተያየቶችን ተለዋውጠዋል።
🟠 ፕሬዝዳንቶቹ ንግግራቸውን አዎንታዊ እና ፍሬያማ ሲሉ ገልጸውታል።
🟠 መሪዎቹ በዩክሬን ጉዳይ ላይ በከፍተኛ ደረጃ እና በሌሎች መንገዶች ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X