የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሰማያዊ ኢኮኖሚ በዓመት እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር ሊያመነጭ እንደሚችል ጠቆመ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሰማያዊ ኢኮኖሚ በዓመት እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር ሊያመነጭ እንደሚችል ጠቆመ
የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሰማያዊ ኢኮኖሚ በዓመት እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር ሊያመነጭ እንደሚችል ጠቆመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.06.2025
ሰብስክራይብ

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሰማያዊ ኢኮኖሚ በዓመት እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር ሊያመነጭ እንደሚችል ጠቆመ

በአፍሪካ ችግሮችን በመረጃ ላይ በተመሠረተ ትንተና እና ምክክር የመፍታት ግብ ያነገበው ዳካርን መቀመጫው ያደረገው ፋውንዴሽኑ የአህጉሪቱ ሰማያዊ ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት በዓመት 300 ቢሊየን ዶላር ገደማ እንደሚያመነጭ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።

"አፍሪካ ከ30 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር በላይ ያልተነካ ለአሳ ኢንዱስትሪ የሚሆን የባሕር ዳርቻ አላት፤ ይህም ከአጠቃላይ የባሕር ዳርቻዋ ወደ 98% የሚሆነው ነው" ሲል ጥናቱ አመላክቷል።

የአፍሪካ ሀገራት በየዓመቱ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመት የዓሳ ምርቶችን እንደሚገዙ እና አብዛኛው ከውጭ የሚገባ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ሱዳናዊ-ብሪታንያዊው የንግድ ሰው ሞ ኢብራሂም ከግንቦት 24–26 በማራኬሽ በተካሄደው የኢብራሂም አስተዳደር ሳምንት ጉባኤ ላይ "በራሳችን ሀብት መተማመን አለብን። [...] አህጉራችን እጅግ ሀብታም ብትሆንም እኛ በጣም ድሆች ነን። ለምን? ሀገሮቻችንን፣ ሀብታችንን እና ህሕቦቻችንን በአግባቡ እያስተዳደርን ስላልሆነ ነው" ብለዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0