ፑቲን በኩርስክ እና ብራያንስክ ክልሎች በተካሄዱ የሽብር ጥቃቶች ዙሪያ የተናገሩት፦

ሰብስክራይብ

ፑቲን በኩርስክ እና ብራያንስክ ክልሎች በተካሄዱ የሽብር ጥቃቶች ዙሪያ የተናገሩት፦

▪ የኪዬቭ ሕገ-ወጥ አገዛዝ ወደ አሸባሪ ድርጅትነት እየተቀየረ ነው የሚለው የሩሲያ ፍራቻ በሲቪሎች ላይ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ተረጋግጧል፣

▪ የኪዬቭ ደጋፊዎች የሽብር ተባባሪዎች ናቸው፣

▪ የዛሬዋ ዩክሬን ሰላም አትፈልግም፤ ሥልጣን ለኪዬቭ ከሕዝብ ይበልጣል፣

▪ በጦር ግንባሩ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እየገጠማት በመሆኑ ኪዬቭ ወደ ሽብር ጥቃቶች ፊቷን አዙራለች፤ ዩክሬናውያን ድርድሮችን እያደናቀፉ እና በሩሲያ ላይ የሽብር ጫና እያሳደሩ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እየጠየቁ ነው፣

▪ የዩክሬን ኃይሎች በጦር ሜዳ በሽንፈት ላይ ሽንፈት እየተከናነቡ ነው፤ በኩርስክ ክልል ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል፣

▪ ፑቲን የኪዬቭን የመሪዎች ግኑኝነት ጥያቄ በተመለከተ "በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማውራቱ ምን ይጠቅማል፤ ከአሸባሪዎች ጋር ማን ይደራደራል?" ብለዋል።

▪ የውጊያ እረፍት ኪዬቭን ለማስታጠቅ፣ የግዳጅ ምልመላ ለማስቀጠል እና የሽብር ጥቃቶችን ለማቀነባበር ጥቅም ላይ ይውላል፤

▪ የኪዬቭ ባለሥልጣናት መሠረታዊ የፖለቲካ ባሕል አያውቁም፣ በሚደራደሩት ወገን ላይ ቀጥተኛ ስድቦችን ይሰነዝራሉ፣

▪ ፕሬዝዳንቱ በብራያንስክ እና ኩርስክ ክልሎች ፍንዳታዎች ለተጎዱ ፈጣን ማገገምን ተመኝተው አስፈላጊ እርዳታ እንዲያገኙ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0