የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ እና የሩሲያ ከፍተኛ ተደራዳሪ ሜዲንስኪ በኢስታንቡል ውይይቶች ዙሪያ ለፑቲን ካቀረቡት ሪፖርት የተገኙ ቁልፍ መግለጫዎች፡-
17:48 04.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 04.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ እና የሩሲያ ከፍተኛ ተደራዳሪ ሜዲንስኪ በኢስታንቡል ውይይቶች ዙሪያ ለፑቲን ካቀረቡት ሪፖርት የተገኙ ቁልፍ መግለጫዎች፡-
የሩሲያ ልዑካን ቡድን ቭላድሚር ሜዲንስኪ ያነሷቸው ጉዳዮች፦
▪ሞስኮ እና ኪዬቭ በግጭት አፈታት ዙሪያ ሰነድ ተለዋውጠዋል፤ "ኳሱ አሁን በዩክሬን ሜዳ ላይ ነው"፣
▪ኪዬቭ በውይይቱ ላይ አቋምን ደግማ ገልጻለች - በ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት በመጀመር ለሁለቱ ሀገራት መሪዎች ግኑኝነት መዘጋጀት፣
▪የሰብዓዊ ጉዳይ "ከድርድሩ ጎን የተደረገ ነበር"፣
▪ሁለቱ ወገኖች በመጀመሪያ - የቆሰሉ፣ በጠና የታመሙ፣ ከ25 ዓመት በታች የሆኑ የጦር እስረኞች ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል፣
▪ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የጦር እስረኞች ልውውጥ ከግንቦት 30-ሰኔ 2 ድረስ ለማካሄድ ዝግጁ ነች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፡-
ዘለንስኪ የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎችን ለመሰብሰብ የሩሲያን የሁለት-ሶስት ቀን ጦርነትን የማቆም ጥያቄ ባለመቀበሉ ስህተት ሰርቷል፣
▪የሩሲያ እና ዩክሬን ልዑካን ስብሰባ ጠቃሚ እና ፍሬያማ ነበር፤ የድርድር ሂደቱ እየሠራ ነው፣
▪ሁለቱም ዙር ቀጥተኛ የሩሲያ-ዩክሬን ውይይቶች ተጨባጭ ውጤቶችን አስገኝተዋል፣
▪ውይይቶችን ለማደናቀፍ ለታለሙ ቅስቀሳዎች አለመሸነፍ አስፈላጊ ነገር ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X