በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ
16:31 04.06.2025 (የተሻሻለ: 16:54 04.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ
ግንባታው ከ20 ሺህ ካ.ሜ በላይ መሬት ላይ እንደሚያርፍ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር በማሕበራዊ ገጹ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል፡፡
2ኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከሉ አርብቶ አደሩ እና ነጋዴው ያለደላላ ጣልቃ ገብነት በቀጥታ የሚገበያዩበት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን ለቁም እንሰሳትና ስጋ ላኪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የአቅርቦት ምንጭ ይሆናልም ተብሏል።
ማዕከሉ በዓለም ባንክ ድጋፍ እንደሚገነባና በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች 6 የሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላትን ለመገንባት የተያዘው ዕቅድ አካል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X