ኢትዮጵያ ለ6 ወር የሚቆይ የአካባቢ ብክለትን የመከላከል ዘመቻ ልትጀምር ነው
14:55 04.06.2025 (የተሻሻለ: 15:04 04.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለ6 ወር የሚቆይ የአካባቢ ብክለትን የመከላከል ዘመቻ ልትጀምር ነው
ግንቦት 30 በሚጀመረው ንቅናቄ ከ15 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ ገልፀዋል።
"ፅዱ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ዘመቻ የከተሞች የድምጽ ብክለትን፣ የፕላስቲክ ብክለትን፣ የአፈርና የውሃ ብክለትን እንዲሁም የአየር ብክለትን መከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።
ንቅናቄው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X