አፍሪካ በባርነት ንግድ ለደረሰባት በደል ፍትሕ ማግኘት አለባት ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በባርነት ንግድ ለደረሰባት በደል ፍትሕ ማግኘት አለባት ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ
አፍሪካ በባርነት ንግድ ለደረሰባት በደል ፍትሕ ማግኘት አለባት ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.06.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ በባርነት ንግድ ለደረሰባት በደል ፍትሕ ማግኘት አለባት ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ

በአፍሪካ የተቋማት ግንባታ ከቅኝ ግዛትም ሆነ በሗላ ጠንካራ አልነበረም የሚሉት የፌዴራል ፍትሕና የሕግ ጥናትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ማዳ ናቸው፡፡

ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ይህ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያሻው ተናግረዋል፡፡

“አሁን ባለው ሁኔታ እነሱ መሳሪያ አድርገው በሚዘውሯቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኩልም ሆነ ራሳቸው ሀገራቱ በቀጥታ በቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት ላይ ተጽዕኖዎችንና በደሎችን የማድረስ ሁኔታ አለ፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ከነጻነት በኋላም አሁንም ቅኝ ግዛታቸው እንደሆኑ አድርገው የሚያስቡና በእዛ እሳቤ የሚንቀሳቀሱ ሀገራት አሉ፡፡”

አፍሪካ ድምጿ፣ ፍላጎቶቿ እና ጥያቄዎቿ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጣችው በዓለም አቀፍ መድረኮች ቁልፍ ተዋናይ መሆን አለባት በሚሉ ሙግቶች አቶ ምትኩ ይስማማሉ፡፡

“አፍሪካ [በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት] ቋሚ መቀመጫ የምታገኝ ከሆነ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን ከሚኖራቸው ጋር እኩል ተሰላፊ ስለምትሆን፤ አህጉሪቱን በሚመለከቱ ጉዳዮችና ውሳኔዎች የአፍሪካውያንን ጥቅም በማስጠበቅ እንዲሁም የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችም ሆኑ የሌሎችን ተጽዕኖ ከመከላከል አንጻር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ቀድሞ የነበሩት በደሎች፣ ጠባሳዎች የሚካሱበትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የአፍሪካ ሕብረት መሪ ቃል አድርጎ የያዘውን ፍትሕ የማስገኘት ጉዳይ አጅንዳ እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ እድል ይኖረዋል፡፡”

አክለውም እንደ ብሪክስ ያሉ ተቋማት የአፍሪካ ሀገራት የካሳ ጥያቄ እንዲመለስ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0