የማሊ የጸጥታ ኃይሎች በቲምቡክቱ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ከተፈጸመ ጥቃት ጋር በተያያዘ 31 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
18:36 03.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 03.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማሊ የጸጥታ ኃይሎች በቲምቡክቱ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ከተፈጸመ ጥቃት ጋር በተያያዘ 31 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
የማሊ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ቢሮ እንዳስታወቀው ሰኞ ዕለት ታጣቂዎች በማዕከላዊ ማሊ የሚገኘውን የሼክ ሲዲ በካዬ ወታደራዊ ካምፕ ለመቆጣጠር እና የቲምቡክቱ አየር ማረፊያ ለመግባት ሞክረዋል።
ታጣቂዎቹ በመኪና ውስጥ የደበቁትን ቦምብ ማፈንዳታቸው ተዘግቧል። የጦር ሠራዊት ክፍሎች ከአጥቂዎቹ ጋር ተኩስ ተለዋውጠው መልሰዋቸዋል የተባለ ሲሆን በግጭቱ አስራ አራት አሸባሪዎች ተገድለዋል።
የጸጥታ ኃይሎች የታጣቂዎቹን መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎችም ይዘዋል። ግንቦት 25 ከሰዓት በኋላ የጦር ሠራዊት ክፍሎች በቲምቡክቱ ያለውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል።
በማሊ ባለሥልጣናት እና በአክራሪና ተገንጣይ ቡድኖች መካከል ያለው የትጥቅ ግጭት የጀመረው እ.ኤ.አ በ2012 ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሀገሪቱ በተለይም ከጸጥታ እና ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አንፃር ችግር ውስጥ ትገኛለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X