ሩሲያ የእህል ገበያ ማቋቋምን በተመለከት ከብሪክስ ሀገራት ጋር ተጨባጭ ድርድር ለማድረግ እንዳቀደች ገለጸች
17:49 03.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 03.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ የእህል ገበያ ማቋቋምን በተመለከት ከብሪክስ ሀገራት ጋር ተጨባጭ ድርድር ለማድረግ እንዳቀደች ገለጸች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የእህል ገበያ ማቋቋምን በተመለከት ከብሪክስ ሀገራት ጋር ተጨባጭ ድርድር ለማድረግ እንዳቀደች ገለጸች
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ፓትሩሼቭ የፕሬስ አገልግሎት እንዳስታወቀው አዲሱ የብሪክስ የእህል ገበያ
🟠 ገለልተኛ የግብርና ምርቶች ዋጋ መለኪያዎችን ይፈጥራል፣
🟠 በምዕራባውያን የንግድ መድረኮች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣
🟠 የእህል ገበያውን ውጤታማነት ለማሳደግ መሠረተ ልማት ያዳብራል።
ተነሳሽነቱ ለብሪክስ አባላት ትክክለኛ ዓለም አቀፍ የዋጋ ግምት ለማቅረብ ያለመ ነው።
የሩሲያ የእህል ገበያ የማቋቋም ሐሳብ ጥቅምት 2017 ዓ.ም በካዛን በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጸድቋል። ተነሳሽነቱ በብሪክስ ሀገራት ውስጥ የእህል ንግድ መድረክ መፍጠርና ሌሎች የግብርና ዘርፎችንም የማካተት ውጥን አለው።
እንደ የሩሲያ የእህል ላኪዎችና አምራቾች ማኅበር ከሆነ በዚህ ገበያ የግብርና እና ተያያዥ ምርቶች የንግድ ልውውጥ መጠን ከ1 ትሪሊዮን ዶላር ሊበልጥ ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X