ናሚቢያ የመከላከያ ሠራዊት 35ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አከበረች
17:15 03.06.2025 (የተሻሻለ: 17:54 03.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናሚቢያ የመከላከያ ሠራዊት 35ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አከበረች
የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥ ፕሬዝዳንት ናንዲ-ንዳይትዋ ግንቦት 24፣ 1983 ዓ.ም በሳም ኑጆማ የተመሠረተውን የናሚቢያ የመከላከያ ሠራዊት አወድሰዋል።
🪖 የሠራዊቱን ሙያዊ ዕድገት እና በሀገር አንድነት ውስጥ ያለውን ሚና አሞካሽተዋል። አባላቱ ኩሩ፣ አንድነት ያላቸው እና ፅኑ ሆነው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ አገልግሎቱ ቁርጠኝነት እና መስዋዕትነት እንድሚጠይቅ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የናሚቢያ ፕሬዝዳንት የሠራዊት አባላቱ አደጋዎች ሲከሰቱ ሲቪሎችን በመርዳት እና ለዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ያደረጉትን አስተዋፅኦ አድንቀዋል።
ፕሬዝዳንቷ ለ14 የጦር ጄኔራሎች የላቀ አገልግሎት ሜዳሊያዎችን ሰጥተዋል። በዓሉ በጦር ጄቶች ትርዒት እንዲሁም በወታደራዊ መሳሪያዎች እና ሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ሰልፍ ተጠናቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ