ተቆጣጣሪዎች ምርምሮችን ከስታርሊንክ ሳተላይት ጣልቃገብነት ሊጠብቁ እንደሚገባ የደቡብ አፍሪካ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አሳሰቡ
12:57 03.06.2025 (የተሻሻለ: 14:04 03.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱተቆጣጣሪዎች ምርምሮችን ከስታርሊንክ ሳተላይት ጣልቃገብነት ሊጠብቁ እንደሚገባ የደቡብ አፍሪካ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አሳሰቡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ተቆጣጣሪዎች ምርምሮችን ከስታርሊንክ ሳተላይት ጣልቃገብነት ሊጠብቁ እንደሚገባ የደቡብ አፍሪካ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አሳሰቡ
ተመራማሪዎቹ እንደ ስታርሊንክ ያሉ ዝቅተኛ የምሕዋር ሳተላይቶች ከደቡብ አፍሪካው ኤስኬ-ሚድ እና ከአጋሩ የአውስትራሊያ ቴሌስኮፕ የሚመጡ ስስ ሲግናሎችን ሊያስተጓጉሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
ሳይንቲስቶቹ ሲግናሎችን ለማሰራጨት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁልፍ ፍሪኩዌንሲዎች ላይ ስስ ሲግናሎች ሊፈጥሩት የሚችሉትን መስተጓጎል ለመገደብ የፈቃድ አሰጣጥ ሕግ ሊበጅ እንደሚገባ ግፊት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም የዓለም አቀፉ የስነ ፈለክ ህብረት (አይ ኤ ዩ) የጨለማ እና የሰማይ ጸጥታ ጥበቃ ማዕከል ተባባሪ ሊቀመንበር ፌዴሪኮ ዲ ቭሩኖ ተናግረዋል።
ይህም እንደ ስፔስ ኤክስ ያሉ ኩባንያዎች የሳተላይት ጨረሮች አቅጣጫቸውን እንዲያዞሩ አሊያም በወሳኝ ምልከታዎች ወቅት ስርጭታቸውን እንዲያቆሙ ሊያስገድድ ይችላል።
ግዙፍ የሬዲዮ ቴሌስኮፖችን የሚገነባው እና ሥራቸውን የሚመራው በምጻረ ቃል ኤስ ኬ ኤ የተሰኘው የጠፈር የምልከታ ማዕከልም እንደ አማዞን እና ዋን ዌብ ካሉ የሳተላይት ኦፕሬተሮች ተመሳሳይ ጥበቃ አንዲደረግለት መጠየቁ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X