የቱኒዚያ ብሪክስን የመቀላቀል ፍላጎት መጨመሩ ተገለጸ
19:07 02.06.2025 (የተሻሻለ: 19:24 02.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቱኒዚያ ብሪክስን የመቀላቀል ፍላጎት መጨመሩ ተገለጸ
የዓለም የጂኦፖለቲካ ምኅዳር መቀየሩን ተከትሎ አንዳንድ ሀገራት የአሜሪካ አግላይ አካሄድ እንዲስተካከል እንዲሁም ኢኮኖሚያቸውን የሚደግፍ አማራጭ የትብብር መድረክ ለማግኘት አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎችን በመቀላቀል ላይ መሆናቸውን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ማህር ኮአይዳ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በቱኒዚያ በመጪው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ላይ ሐሳባቸውን የሰጡት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው፤ የአሜሪካ የታሪፍ ጭማሪ እና የምትከተለው ጥብቅ ፖሊሲ ዓለም አቀፉ ነፃ የንግድ ሥርዓትን በማናጋት እንደ ቱኒዚያ ባሉ ሀገራት ላይ አዳዲስ መሰናክሎችን መፍጠሩን አብራርተዋል።
የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ የትብብር መድረኮችን ማብዛት በፈተና ላይ ለሚገኘው የቱኒዚያ ኢኮኖሚ ወሳኝ መሆኑን በማንሳትም፤ በተለይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ጋር ሀገሪቱ ያለት ንግግር በቆመበት፣ የህዝቡ የፋይናንስ አቅም እና የኢንቨስተሮችን እምነት በተሸረሸረበት በዚህ ወቅት የትብብር መድረኮችን ማብዛት አማራጭ ያለው ጉዳይ አለመሆኑን ገልጸዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X