ከኢስታንቡል ንግግሮች በኋላ ሜዲንስኪ የተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፦

ከኢስታንቡል ንግግሮች በኋላ ሜዲንስኪ የተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 ሩሲያ ለዩክሬን ሁለት ክፍል ያለው ረቂቅ ሰነድ አስረክባለች።
🟠 የሩሲያ ሰነድ ሁለተኛ ክፍል በተኩስ አቁም ዙሪያ በርካታ አማራጮችን አቅርቧል።
🟠 ሩሲያ በራሷ ተነሳሽነት 6 ሺህ የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለዩክሬን ታስረክባለች።
🟠 ሩሲያ እና ዩክሬን በጠና የታመሙ እና የቆሰሉ ወታደሮችን ይለዋወጣሉ።
🟠 ሩሲያ እና ዩክሬን በጠና የቆሰሉ ወታደሮችን ለመለዋወጥ የህክምና ኮሚሽኖች ያደራጃሉ፤ ልውውጡ መደበኛ ይሆናል።
🟠 ሩሲያ የሟቾችን አስከሬን ለመሰብሰብ በተወሰኑ የጦር ግንባሮች ላይ ለ2-3 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ሃሳብ ለዩክሬን አቅርባለች።
🟠 ሩሲያ እየገፋች በመሆኑ በጦር ሜዳው የምቱ በርካታ የዩክሬን ወታደሮች ይገኛሉ።
🟠 ዩክሬን በሩሲያ የቀረበውን የተኩስ አቁም ሀሳብ እንደምትገመግም ገልፃለች።
🟠 ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የህፃናትን ጉዳይ ተወያይታለች፤ ሜዲንስኪ በዩክሬን የተላለፉ 339 የህፃናት ስም ዝርዝር አሳይተዋል።
🟠 ሩሲያ ከወላጆቻቸው ጋር የተለያዩ ህፃናትን ጉዳይ ትመለከታለች።
🟠 በቅርቡ ከሩሲያ 101 ህፃናት በዩክሬን በኩል ደግሞ 20 የሚጠጉ ህፃናት ተመልሰዋል።
🟠 ልክ እንደ ሶቪየት ወታደሮች የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ህፃናትን በተመለከተ በኃላፊነት ይንቀሳቀሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X