በመላው ዓለም የሚገኙ የናማ ሕዝቦችን አንድ ለማድረግ የወጠነው 'ናማ ፌስቲቫል' እየተካሄደ ነው
12:29 02.06.2025 (የተሻሻለ: 12:44 02.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበመላው ዓለም የሚገኙ የናማ ሕዝቦችን አንድ ለማድረግ የወጠነው 'ናማ ፌስቲቫል' እየተካሄደ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በመላው ዓለም የሚገኙ የናማ ሕዝቦችን አንድ ለማድረግ የወጠነው 'ናማ ፌስቲቫል' እየተካሄደ ነው
ዓመታዊው የናማ የባህል ፌስቲቫል "የናማ ህዝቦች ለውጥ፣ ዕድገት እና ዘላቂነት ይሻሉ" በሚል መሪ ሐሳብ ለ6ኛ ጊዜ በናሚቢያ ኬትማንሾፕ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ፌስቲቫሉ የናማ ሕዝቦችን ቅርስ ለመዘከር እንዲሁም ዓለም አቀፉን ማኀበረሰብ ወደ አንድ ለማምጣት መወጠኑን የፌስቲቫሉ ሊቀ-መንበር ዲርክ ኢገብ ተናግረዋል።
ሊቀመንበሩ "ሰዎች እርስ በእርሳቸው ሲደጋገፉ ሁሉም ሰው በመንፈስ እና በስሜት የሚያድግበት ነባራዊ ሁኔታ ይፈጠራል። በጉዟችን ውስጥ ሁላችንም የተያያዝን መሆናችንን ማጉላት ይገባል" ብለዋል።
በተጨማሪም የናማ ማኀበረሰብ ከሁሉም ህዝቦች ዘላቂ እንክብካቤ እና ቁርጠኝነትን እንደሚፈልግም ገልጸዋል።
የኬትማንሾፕ ከንቲባ አናሊዝ ክናውስ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ "ከክብረ በዓልነት ባለፈ ታሪክን በአዛውንቶች ተረክ፣ በባህላዊ ጭፈራ እንዲሁም በኪነ-ጥበብ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፊያ መድረክ ሆኖ ያገለግላል" ብለዋል።
አክለውም እውነተኛ ክብር የሚገኘው ባህልን ከማሳየት ባለፈ መሬትን፣ የኢኮኖሚያ ኃይልን እና ተገቢ ማኀበራዊ ስፍራን በማግኘት እንደሆነ አጽዕኖት ሰጥተዋል።
እ.አ.አ ግንቦት 28 ቀን 2025 የጀመረው የባህል ፌስቲቫሉ እስከ ሰኔ 6 እንደሚቆይም ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
