አምስት የአፍሪካ ሀገራት ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 16 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአምስት የአፍሪካ ሀገራት ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 16 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ አደረጉ
አምስት የአፍሪካ ሀገራት ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 16 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.06.2025
ሰብስክራይብ

አምስት የአፍሪካ ሀገራት ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 16 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ አደረጉ

አስተዋጽኦው ለአህጉሪቱ ልማት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በ220 በመቶ መጨመሩን የሚያመለክት ነው።

ጋና አምስት ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ በማድረግ በመምራት ላይ ትገኛለች።

ሱዳን፣  ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን እያንዳንዳቸው ሶስት ሚሊየን ዶላር አዋጥተዋል።

 ጋሚቢያ በበኩሏ ሁለት ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ አድርጋለች።

ይህ ልገሳ ከዚህ ቀደም ከገቡት ቃል በሦስት እጥፍ እንደሚበልጥና የአፍሪካን አብሮነትና የፋይናንስ ነፃነት የሚያሳይ ነው ሲል የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

"አፍሪካ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን የራሷንም የወደፊት እጣ ፈንታ ትቀርጻለች" ሲሉ በአፍሪካ ልማት ባንክ የሀገራቱ ተወካይ ሩፉስ ዳርኮርቴይ ተናግረዋል።

ውሳኔው የተገለጸው ባሳለፍነው ሳምንት በአቢጃን በተካሄደው የአፍሪካ ልማት ባንክ የ2025 ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0